+2510582207991 abayplc2021@gmail.com
የአከባቢ ጨረታ ማስታወቂያ የአገለገሉ እቃዎች ሽያጭ የጨረታ ቁጠትር አኮኃ/አጨ/04/17
ቀን 25/02/2017 ዓ.ም
ኩባንያችን አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህር በኩባንያው አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ የኮንስትራክሽን እቃዎች (የመጠጥ ውሃ መገጣጠሚያ እቃዎች ) ፣ የቢሮ መገልገያ እቃዎች እና የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በአካባቢ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከላይ የተቀሱትን ያገለገሉ እቃዎችን ተወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ የአካባቢ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ የኩባንያችን ቢሮ በመገኘት (ቢሮ ቁጥር 19 ) ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ የአገለገሉ እቃዎች ሽያጭ ጨረታ ተብሎ ትክክለኛ ስምና አድራሻ እንዲሁም ስልክ ቁጥር በመጻፍ አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ ቁጥር 19 ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ባህርዳር በሚገኘው የኩባንያው ዋና መ/ቤት ግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 19 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የአካባቢ የሽያጭ ጨረታው በአስረኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የአጠቃላይ ዋጋውን 1% የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ወይም የባንክ ዋስትና በኩባንያው ስም ማለትም በአባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው
- የጨረታ አሻናፊ ማሸነፉ ከተገለጸለት ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያ ኩባንያው በሚያሳውቀው የባንክ አካውንት ገቢ በማድረግ የአሸነፉባቸውን እቃዎች ማንሳት አለባቸው ፡፡
- በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም
- ኩብንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል
አድራሻ
ቀበሌ 16 ህዳሴ ሰፈር ፊትለፊት
የፓምፕ፣ ጀነሬተር፣ ኤችዲፒ ፓይፕ፤ የዉሃ እቃዎች እና የዉሃ ቦቴ ኪራይ አገልግሎት ግዥ ብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ሰነድ
ጥቅምት/2017 ዓ.ም ፓምፕ፣ ጀነሬተር፣ ኤችዲፒ ፓይፕ እና የዉሃ እቃዎች ግዥ ብሄራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር አኮኃ/ብግጨ/005/17
አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚዉል ፓምፕ፣ ጀነሬተር፣ ኤችዲፒ ፓይፕ እና የዉሃ እቃዎች ግዥ እና የነዳጅ ቦቴ ትራንስፖርት አገልግሎት ኪራይ ግዥ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ድርጅቱ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፤
2. የሚገዙ ዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 16 ህዳሴ ሰፈር ፊት ለፊት አመልድ ጋራጅ ዉስጥ ከሚገኘው አባይ
ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ ከግዥ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 19 የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማግኘት ይቻላል፡፡
4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በአባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም በማሳራት ማስያዝ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመፃፍ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት በስራ ሰዓት ከግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 19 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
6. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ይዘጋል፤ 15 ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 19 ይከፈታል፡፡
7. 15ኛው ተከታታይ ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
9. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም
በስልክ ቁጥር 09 91 02 14 30 በመደወል ወይም በድረገጻችን https://www.abayconstruction.org.et/auctionbid/ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
It is nice!!